በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ለሴክተር መስሪያ ቤት ባለሙያዎች በኮምፒውርና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ስለጠና ሰጥቷል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሀይሉ ዘውዴ የኮምፒዉተር እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም በተመለከተ ስልጠናው ለባለሙያዎች የመንግስትንና የህዝብን ተልእኮ በየዘርፉ በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ አፋጣኝ ምላሾችን ለመስጠትና የኮምፒውተር ክህሎት ይበልጥ ለማዳበር ያግዛል ብለዋል።

ስለጠናውን የሰጡት የጽ/ቤቱ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታና አስተዳደር ዘርፍ ባለሙያ አቶ መሀመድ አደም ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የኮምፒውተር ክህሎት ስልጠና ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል።

ስልጠናው በቀጣይ ለምንሰራቸው ስራዎች እንዲሁም የተለያዩ የኮምፒውተር ብልሽቶችም ቢያጋጥሙን ባለሙያዎችን ባለመጠበቅ በሰለጠነው ልክ ችግሮቻችንን መፍታት የምንችል መሆኑ።

ለስልጠናውን ውጤታማነትና የታሰበውን እውቀትና ክህሎት ለማስገንዘብ እንዲቻል ትኩረት ሰጥተው መከታተል አለባቸው ።

ስልጠናውም ለ21 ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።