የማሕበራዊ ሚዲያ አስተዳዳሪዎች/admin/ እና የጥቃት ተጋላጭነታቸው

የተቋማት ማሕበራዊ ሚዲያ አስተዳዳሪዎች ገጾቻቸው ካላው ሰፊ ተደራሽነት እና ከሚወጡት ሚና አንፃር በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የረጅም ጊዜ ቆይታ ስለሚኖራቸው ለተለያዩ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ።
በተለይ የተቋማት የማህበራዊ ሚዲያ አስተዳዳሪዎች ሊያጋጥሟቸው ከሚችሉት የሳይበር ጥቃት ዓይነቶች መካከል የሚከተሉት የተለመዱት ናቸው፡፡

ማልዌር እና ስፓይዌር
መረጃን ለመስረቅ ወይም የአስተዳዳሪውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የተነደፉ ተንኮል አዘል ሶፍትዌሮች ሲሆኑ ብዙውን ጊዜ በተንኮል አዘል ሊንኮች ወይም አታችመንቶች ይሰራጫሉ።

የማስገር (Phishing) ጥቃቶች
ጥቃት ፈጻሚዎች የማሕበራዊ ሚዲያ አስተዳዳሪዎችን የይለፍ ቃል ወይም ሚስጥራዊ መረጃ ለማግኘት የማታለያ ኢ-ሜይሎችን፣ የተለያዩ መልዕክቶችን ወይም ድረ-ገጾችን ይጠቀማሉ።
ምሳሌ ፦ እንደ ፌስቡክ ወይም ኢንስታግራም ላሉ ገጾች አስተዳዳሪው ስለአካውንቱ መረጃን እንዲሰጥ ወይም እንዲያረጋግጥ የሚጠይቅ ኢ-ሜይል ሊሆን ይችላል።

የማሕበራዊ ሚዲያ ገጽን መውረስ (የይለፍ ቃል ጥቃቶች)
ጥቃት ፈጻሚዎቹ የተሰረቁ ወይም የተገመቱ የይለፍ ቃላትን በመጠቀም የማሕበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን ይቆጣጠራሉ።
ይህ በመሆኑ አስተዳዳሪዎቹ አካውንቶቻቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው ሀሰተኛ መረጃ በአካውንታቸው ላይ ሊሰራጭ ይችላል።

ማህበራዊ ምህንድስና
ጥቃት ፈጻሚዎች የማህበራዊ ሚዲያ አስተዳዳሪዎችን በማህበራዊ ምህንድስና (ለምሳሌ የሥራ ባልደረባ ወይም የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ መስሎ በማታለል) የይለፍ ቃል ወይም ሌላ መረጃ በመጠየቅ የሳይበር ጥቃት ሊፈጽሙ ይችላሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *