እንኳን ደህና መጡ!

በዲጂታል የበለጸገች ኢትዮጵያን በጋራ እንፍጠር!

የምስራቅ ጉራጌ ዞን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ

በሳይንስና ቴክኖሎጂ የበለጸገ ማህበረሰብ ለሀገር ብልጽግና!

ወ/ሮ ልኬለሽ ከበደ ተክሌ

ሳይንስና ኢንፎርመሽን ቴክኖሎጂ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከምንም በላይ መሆኑን ዛሬ ላይ የስልጣኔ ጫፍ የደረሱ፣ የበለፀጉና የዓለማችን ሃያላን ተብለው የሚጠሩ አገሮች ምሥክሮች ናቸው። ይህም በመሆኑ መንግስት የሀገራችን ሕዝብ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆንና የቴክኖሎጂው ሽግግር ከጫፍ እንዲደርስ ተግቶ በመሥራቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀላል የማይባል የሀገራችን ሕዝብ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን ችሏል። ለዚህም ማሳያ መሆን የሚችሉ በርካታ ተግባራትን መጥቀስ የሚቻል ሲሆን በክልላችን የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከሚመለከታቸው መ/ቤቶች ጋር በመሆን በአያሌ የገጠር ቀበሌያትና ወረዳዎች የገጠሩ ሕብረተሰብ ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ከሌሎች የመረጃ ምንጮች የሚፈልጓቸውን መረጃዎች በተለያዩ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች አማካይነት ማግኘት እንዲችሉ የማህበረሰብ መረጃ ማዕከላትን አቋቁሞ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሽቦ አልባ ስልኮችም በብዙ የገጠር ቀበሌያት በቢሮውና አግባብነት ባላቸው ተቋማት በኩል የተሠራጩ ሲሆን እስኩል ኔትና ወረዳ ኔቶችም እንዲሁ የሚጠቀሱ ናቸው። እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልል ማዕከል፣ በዞኖች፤ በልዩ ወረዳዎች በወረዳዎችና በከተማ አስተዳደሮች የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ደረጃ በደረጃ እየተዘረጋ ያለ ሲሆን በዋናነት የመንግስት መረጃ ሥርዓት የማሳለጥ፣የቪዲዮ ኮንፍረንስ አገልግሎት በመስጠት ፈጣን የሆነ መረጃ እንዲዳረስ የማድረግና የማህበረሰብ መረጃና ሬድዮ አገልግሎት በመስጠት በርካታ ወጣቶችን በማደራጀትና በማሰልጠን ወደ ስራ እያስገባ ይገኛል። ባለፉት ዓመታት በኢኮ ዘርፍ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ ተመራቂዎችን በማህበር በማደራጀት የተለያዩ ድጋፎችን ማለትም ስልጠና፣ የገበያ ማፈላለግና የማማከር አገልግሎት በመስጠት የግል ካምፓኒ ፈጥረው ወደ ንግድ ዓለም እንዲገቡ እየተደረገ ይገኛል። ከዚህም በተጨማሪ የቢሮውን ዌብ ሳይት በማልማት እና የፌስቡክ ገጽ በመክፈት እንዲሁም የተለያዩ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በተቋማችን አጠቃላይ አፈጻጸምና ሁኔታ ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እተከናወነ ይገኛል። በመሆኑም መምሪያው ከዞን እስከ ወረዳ/ከተማ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶችን ከመዘርጋት፣ ከማስፋፋትና ክህሎትን ከማዳበር አንፃር ያከናወናቸው አበረታች ተግባራት ቀጣይነት እንዲኖራቸው ባለድርሻ አካላት ዘርፉ በክልላችን በከፍተኛ ደረጃ እንዲበለጽግና ሕዝባዊ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲረጋገጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ ይጠበቃል። ከሳይንስና ፈጣራ ስርጸት አንጻር በየአከባቢው ያሉ እንቅስቃሴዎችን በማበረታታት የዜጎች የመገናኘት ሁኔታ በማሳለጥ ምርታማነትንና ተጠቃሚነትን ለመጨመር የሚያስችል ተግባር በመፈጸም ከዘርፉ ይገኛል ተብሎ የታቀደውን ግብ ለማሳካት ርብርብ የሚደረግ ይሆናል። ስለዚህ በዞናችን የሚገኙ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ት/ቤቶች፣ የከተማና የገጠር ነዋሪዎች በሙሉ ሀገራችን አድገ ወደ ታቀደው ስፍራ ለመድረስ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን አማራጭ የሌለው መንገድ መሆኑን ተገንዝበው ጥያቄዎችን በራስ ተነሳሽነት ጭምር በማቅረብ እና ከመምሪያው ጋር በቅርበት በመስራት የታቀደው ግብ ላይ ለመድረስ ሁላችንም የበኩላችንን እንድንወጣ ከአደራ ጭምር አሳስባለሁ፡፡

እኛ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

የቢሮ ማሽኖች ጥገና

ለተለያዩ ተቋማት የቢሮ ማሽን (ኮምፕተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ፎቶ ኮፒ ማሽኖች እና ለሎችም) የሃርድዌርና ሶፍትዌር ጥገና እንሰጣለን

የተለያዩ የክህሎት ስልጠና መስጠት

በተለዩ ክፍተቶች ላይ ለመንግስት ሰራተኞች የክህሎት ሥልጠና መስጠት በተጨማሪም የተግባር ወይንም የሥራ ላይ ሥልጠና ለተማሪዎች መስጠት

ኔትወርክ መዘርጋትና ማዋቀር

በኔትወርክ መሠረተ ልማት ላይ ለተለያዩ ተቋማት የዝርጋታ፣ የማዋቀርና የማማከር አገልግሎት እንሰጣለን

ማህበረሰብ መረጃ ማዕከላትን ድጋፍ ማድረግ

በዞኑ ውስጥ ያሉ ማህበረሰብ መረጃ ማዕከላትን ድጋፍ ክትትል ማድረግ እንዲሁም የተደራጁ መረጃ ማዕከላትን ማጠናከር

ሶፍትዌርና ድረ-ገጽ ማልማት

ለተለያዩ ተቋማት አዳድስ ድረገጾችን ማልማትና የማማከር አገልግሎት እንዲሁም በተጨማሪ ለተለያዩ ተቋማት ሶፍትዌሮችን ከስተማይዝ በማድረግ አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል

ለተለያዩ ፈጠራ ሥራዎች ድጋፍና ክትትል ማድረግ

አዳዲስ ፈጠራ ሥራዎችን መለየትና ለተለዩ ፈጠራዎች ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንዲሁም አዕምሯዊ መብት ጥበቃ እንዲደረግ ፈጠራዉን ማስመዝገብ

አዳዲስ ዜናዎች

˝በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 7ኛው ዙር ሀገራዊ የአረንጓዴ ዐሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ዶቦ ጡጦና በሬሳ ቀበሌ ላይ በማለዳው ተጀምሯል!!

˝በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 7ኛው ዙር ሀገራዊ የአረንጓዴ ዐሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን…

˝በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 7ኛው ዙር ሀገራዊ የአረንጓዴ ዐሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ዶቦ ጡጦና በሬሳ ቀበሌ ላይ በማለዳው ተጀምሯል!! ( ሐምሌ…

በምስራቅ ጉራጌ ዞን በክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለወጣቶች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በምስራቅ ጉራጌ ዞን በክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለወጣቶች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በምስራቅ ጉራጌ ዞን በክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለወጣቶች ስልጠና እየተሰጠ ነው። ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም (ቡታጅራ) የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ በ2017/18 በጀት አመት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት…

ማይክሮሶፍት ለዊንዶዉስ-10 የሚያቀርበዉን የደህንነት ማሻሻያ ከ4 ወር በኋላ እንደሚያቋርጥ አስታወቀ ።

ማይክሮሶፍት ለዊንዶዉስ-10 የሚያቀርበዉን የደህንነት ማሻሻያ ከ4 ወር በኋላ እንደሚያቋርጥ አስታወቀ ።

ግንቦት 25/2017 ዓ.ም፤ ማይክሮሶፍት ኩባንያ ከጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለዊንዶዉስ 10 ተጠቃሚዎች የሚያቀርበዉን የደህንነት ማሻሻያ ድጋፎችን እንደሚያቋርጥ ገልጿል። ከአራት / 4 /ወር በኋላ የቴክኒክ ድጋፍ እና የሶፍትዌር ዝመናዎችን ለዊንዶዉ-10 ምርቶች…

ስለ ተቋማችን አገልግሎት አስተያየታቸውን የሰጡ

ተቋሙ ለዞኑ በሳይንስና ቴክኖሎጂው ዘርፍ እያበረከተ ላለው ሥራ አድናቆት መስጠት ያስፈልጋል። በተለያዩ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስራዎችን በመጠቀምም ሆነ በመፍጠር ግንባር ቀደም ማኅበረሰብን ለመፍጠር ጉልህ ሚና ያለው ተቋም ነው።

አቶ ሙስጠፋ ሀሰን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ

ተቋሙ ለዞኑ በሳይንስና ቴክኖሎጂው ዘርፍ እያበረከተ ላለው ሥራ አድናቆት መስጠት ያስፈልጋል። በተለያዩ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስራዎችን በመጠቀምም ሆነ በመፍጠር ግንባር ቀደም ማኅበረሰብን ለመፍጠር ጉልህ ሚና ያለው ተቋም ነው።

አቶ ሀሰን ከድር የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ

ከምስል ማኅደሮቻችን