˝በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 7ኛው ዙር ሀገራዊ የአረንጓዴ ዐሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ዶቦ ጡጦና በሬሳ ቀበሌ ላይ በማለዳው ተጀምሯል!!

˝በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 7ኛው ዙር ሀገራዊ የአረንጓዴ ዐሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ዶቦ ጡጦና በሬሳ ቀበሌ ላይ በማለዳው ተጀምሯል!!

˝በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 7ኛው ዙር ሀገራዊ የአረንጓዴ ዐሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ዶቦ ጡጦና በሬሳ ቀበሌ ላይ በማለዳው ተጀምሯል!! ( ሐምሌ 24/2017 ቡታጅራ) ˝በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል እንደ ሀገር 700 ሚሊዮን ችግኞች በመትከል የዘንድሮ ሀገራዊ 7ኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው። አንደ ምስራቅ ጉራጌ ዞን ሀገራዊ ተልዕኮ ለመወጣት ከችግኝ ዝግጅትና አቅርቦት ጀምሮ በርካታ ተግባራት የተከናወኑበት ይህ የአረንጓዴ ዐሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ጀንበር ወጥታ እስከምትጠልቅ ባለዉ ጊዜ በከፍተኛ ትጋት ቀኑን ሙሉ የሚካሄድ መሆኑንም ተገልጾዋል። በዚህም መላው የዞኑ ማህበረሰብ በነቂስ ማልዶ ወጥቶ በአረንጓዴ ዐሻራዉ መስክ ታላቅ የታሪክ ዐሻራ እያኖረ የሚገኝ ሲሆን፤ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ፣ የጥላና የአፈር መሸርሸርን የሚከላከሉ ችግኞች እየተተከሉ ነው። በአጠቃላይ መርሃ – ግብሩ በመትከል ማንሰራራት በሚል እየተካሄደ ሲሆን፤ እንደ ሀገር 700 ሚሊዮን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተተከሉበት የሚገኝበትም ነው።

በምስራቅ ጉራጌ ዞን በክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለወጣቶች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በምስራቅ ጉራጌ ዞን በክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለወጣቶች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በምስራቅ ጉራጌ ዞን በክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለወጣቶች ስልጠና እየተሰጠ ነው። ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም (ቡታጅራ) የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ በ2017/18 በጀት አመት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ከ5000 በላይ ወጣቶች በመሰረታዊ ኮምፒውተር ዕውቀት፣ በኢኮደርስ እና በስፔስ ሳይንስ ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት መጀመሩን አስታወቀ። የመምሪያው ሃላፊ ወ/ሮ ልኬለሽ ከበደ እንደገለጹት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ላይ ተማሪዎች በመሰረታዊ ኮምፒውተር ዕውቀት፣ በኢኮደርስ እና በስፔስ ሳይንስ ስልጠና ተጀምሯል። ወጣቶቹ በክረምቱ በጎ አድራጎት መርሃ ግብሮች እንደሚሰማሩም አስገንዝበዋል። ስልጠናው ከሌሎች የክረምት ትምህርት ጋር አቀናጅቶ የሚሠጥ ሲሆን በአግባቡ ጀምረው ለሚያጠናቅቁ ሠልጣኞች በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ እስፓሻል ኢንስትቲዩት አማካኝነት ሀገር አቀፍ ሠርተፍኬት የሚሠጥ መሆኑንም ሃላፊዋ ተናግረዋል። የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሀይሉ ዘውዴ ትምህርቱ ለተማሪዎች የሚሰጠው ከከፍተኛ ተቋም ዩኒቨርሲቲ በመጡ የበጎ ፈቃድ አድራጊ ተማሪዎች ሲሆን፤ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንደ ተቋም በይፋ መጀመሩን አስረድተዋል። የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብሩ በትኩረትና በትጋት እንዲከናወንም በስፍራው ለተገኙ አካላት አሳስበዋል።

ማይክሮሶፍት ለዊንዶዉስ-10 የሚያቀርበዉን የደህንነት ማሻሻያ ከ4 ወር በኋላ እንደሚያቋርጥ አስታወቀ ።

ማይክሮሶፍት ለዊንዶዉስ-10 የሚያቀርበዉን የደህንነት ማሻሻያ ከ4 ወር በኋላ እንደሚያቋርጥ አስታወቀ ።

ግንቦት 25/2017 ዓ.ም፤ ማይክሮሶፍት ኩባንያ ከጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለዊንዶዉስ 10 ተጠቃሚዎች የሚያቀርበዉን የደህንነት ማሻሻያ ድጋፎችን እንደሚያቋርጥ ገልጿል። ከአራት / 4 /ወር በኋላ የቴክኒክ ድጋፍ እና የሶፍትዌር ዝመናዎችን ለዊንዶዉ-10 ምርቶች እንደማያቀርብ የገለጸዉ ኩባንያዉ የዊንዶውስ-10 ተጠቃሚዎች ቀኑ ከመድረሱ በፊት የዊንዶዉስ-10 ምርቶቻቸዉን ወደ ዊንዶዉስ-11 እንዲያሳድጉ መክሯል። የዊንዶውስ-10 ምርትን እየተጠቀሙ መቆየት ለሚፈልጉ ደንበኞቹ የተራዘመ የደህንነት ማሻሻያ (ESU) ፕሮግራም እንደሚያቀርብ የጠቆመዉ ማይክሮሶፍት ይህ አገልግሎት ግን ክፍያ የሚጠየቅበት ነው ብሏል ። የተራዘመ የደህንነት ማሻሻያ ፕሮግራም ማድረግ የሚፈልጉ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት የዊንዶውስ-10 ምርቶቻቸዉ የደህንነት ማሻሻያ ለማይክሮሶፍት ክፍያ በመፈጸም ብቻ ድጋፉ ሳይቋረጥ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ መጠቀም እንደሚችሉ ገልጿል። ኩባንያው እንዳለው መክፈል የማይችሉ ተጠቃሚዎች ግን ከዊንዶዉ-10 ወደ 11 በነጻ ለመሸጋገር የዊንዶዉስ-ቨርዥን 22H2 ተጠቃሚ መሆንና ዝቅተኛዉን የሃርድዌር ስፔስፊኬሽን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።ይህንንም ለማረጋገጥ የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ማወቅ እንደሚችሉ አብራርቷል። በቅድሚያ Start >Settings > Update & Security > Windows Update በመጨረሻም Check for updates የሚለዉን በመጫን ማረጋገጥ ይችላሉ። በመሆኑም እርስዎ የዊንዶዉስ-10 እና ከዚያ በታች ያሉ ምርቶች ተጠቃሚ ከሆኑና ከፍለዉ የደህንነት ማሻሻያ ካላደረጉ / ካላራዘሙ / በስተቀር የሚጠቀሙበትን የዊንዶዉስ ምርት በማዘመን ከሶፍትዌር ዝመና ጋር በተያያዘ ሊደርስ ከሚችል የሳይበር ጥቃት ራስዎንና ተቋምዎትን እንዲጠብቁ እንመክራለን።