• በዞኑ የሳይንስና የኢንፎርሜሽ ቴክኖሎጂ እንዲስፋፋ ያደርጋል፣ ይደግፋል፣ ያስተባብራል፤
  • ዞናዊ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መማክርት ጉባኤ እንዲቋቋም ያስተባብራል፣ የአሠራር መመሪያው በመስተዳድር ምክር ቤቱ ሲጸድቅ ተግባራዊ እንዲሆን በትኩረት ይሰራል፤
  • የዞኑን የሳይንስና የቴክኖሎጂ ፍላጎት ይለያል፣ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመመካከር ፍላጎቱ የሚሟላበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
  • ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በዞኑ የቴክኖሎጂ ፓርኮች እንዲቋቋሙ ያደርጋል፣
  • የምርምር ፕሮቶኮሎች ሥነ-ምግባር በማዘጋጀት የፈጠራ ሥራዎች በፕሮቶኮል እንዲደገፉ ያደርጋል፣ የሥነ-ምግባር ጉድለት ሲያጋጥም አስፈላጊ የሆነ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፣
  • በዞኑ የሚካሄዱ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ስራዎች እንቅስቃሴዎች የገንዘብ፣ የማቴሪያልና የቴክኒክ ድጋፎች የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ ዘርፎችን ለማዳበር የላቀ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትንና ግለሰቦችን ያበረታታል፣
  • በዞኑ የሚካሄዱ የጥራት መሰረተ ልማት ተግባራትን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ያስተባብራል፣ ጉድለቶች ሲኖሩም ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
  • በዞኑ የሚካሄዱ የጨረራ መከላከያ ስራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ያስተባብራል፣ ጉድለቶች ሲኖሩም ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
  • በምርምር የሚገኙ ወይም የሚፈጠሩ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች የአእምሯዊ ንብረት መብት እንዲያገኙ ድጋፍ ያደርጋል፣
  • የመገናኛና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ጥራታቸው፣ ደህንነታቸውና አስተማማኝነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የሚያስችሉ ደረጃዎችን ይወስናል፣ ተግባራዊ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፣
  • የመንግስት ተቋማት የመረጃ ስርዓትን ከመገንባትና ከማቀናጀት አንፃር የመንግስት የዶሜይን ስም ይደለድላል፣ አድራሻ ይመዘግባል ይቆጣጠራል፣
  • በዞን መንግስት ተቋማት መካከል ዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን መረብ መዘርጋቱ ይከታተላል፣ የሶፍትዌርና የሲስተም ልማት ሥራን ያከናውናል፣ እንዲከናወን ያደርጋል፣ ተገቢውን ድጋፍም ይሰጣል፣ ተግባራዊነቱን ይቆጣጠራል፤
  • በመንግስት ተቋማት መካከል የተቀናጀና ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ፍሰትና ልውውጥ እንዲኖር ድጋፍ ይሰጣል፤ በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋሉን ይከታተላል
  • በየደረጃው ላሉ የመንግስት ተቋማትና የሕብረተሰብ ክፍሎች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጥናት ዲዛይን ያዘጋጃል፣ ዘመናዊ የመረጃ ልውውጥ ፍላጎት ወይም ክፍተት የመለየት ስራ ያከናውናል፣ የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣
  • በዞኑ በየደረጃው ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ውስብስብና መለስተኛ ኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማት ይዘረጋል፣
  • በዞኑ የአስተዳደር እርከኖች የቪዲዮ ኮንፈረንሲንግ፣ የማህበረሰብ የመረጃ ማዕከላትን፣ የጥሪ ማዕከልና የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያዎችን ያቋቁማል፣ ያስተዳድራል፣ ይቆጣጠራል፤
  • የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ የግል ሥራ ፈጠራ ማእከላትን ያቋቁማል፤
  • የዞኑን መረጃ መረብ ዝርጋታ እና ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ሥራን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይቆጣጠራል፣ የሚለሙ ሶፍትዌሮችና አኘሊኬሽኖችን ደረጃ ይወስናል፤
  • በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ላይ የቴክኒክ የስልጠናና መሰል ድጋፎችን ያደርጋል፣ የብቃት ማረጋገጫና ፈቃድ ይሰጣል፣ ተግባራዊነቱንም ይቆጣጠራል፤
  • የዞኑ መንግስት የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን አጠቃቀም ይቆጣጠራል፣ እንዲጠገኑ ያደርጋል፣ ብልሽታቸው ከአቅም በላይ የሆኑትን ያሰውግዳል፣
  • ዓላማውን ለማስፈጸም የሚያግዙ ሌሎች ተዛማጅ ተግባሮችን ያከናውናል፣