የኢኮቴ መሠረተ ልማት ዝርጋታና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

  • በኢኮቴ ዘርፍ ለተሰማሩ ድርጅቶች  አዲስ ፈቃድ መስጠት፤
  • የብቃት ማረጋገጫ መስጠት፤
  • ነባር ፈቃድ እድሳት መስጠት
  • እንደዚሁም ድጋፍና የቁጥጥር ስራዎች የሚሰራበት ነው፡፡
  • 1 በዞን/ በወረዳ/ ከተማ ደረጃ የጥገናና እድሳት፣ማዕከል ማቋቋም
  • እንደዚሁም የስልጠና ማዕከላት ማቋቋም
  • ከባለድርሻ ጋር የግብ ስምምነት በመፈራረም ቅንጃታዊ አሰራርን የማጠናከር ስራ ይሰራበታል ለምሳሌ /ከዩኒቨርሲቲ ፤ከኮሌጆች፤ ከትምህርት፤ ከኢንተርፕራይዝ ፣ከግብርና እዲሁም ከሌሎችም ጋር ይሰራበታል
  • የኢኮቴ መሳሪያዎች ገበያ ላይ ስለ መኖራቸው የዳሰሳ ጥናት የማድረግ ስራ የሰራበታል፡፡
  • በዞኑና በወረዳ/ከተማ ደረጃ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎትና ግንዛቤ ክፍተት ዳሰሳ በማድረግ (ዲጂታል ሊትሬሲ) ወይም የመንግስት ሠራተኞች ስልጠና የመስጠት ስራ ይሰራበታል፡፡
  • በዞኑ ስር ያሉ የማህበረሰብ መረጃ ማዕከላትን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ደረጃቸዉን የማሻሻል ስራ ይሰራበታል፡፡
  • የማህበረሰብ መረጃ ማዕከላት እንዲቋቋምላቸው መስፈርት ያሟሉ መዋቅሮችን በመለየትና ቅድመ ሁኔታዎችን የማመቻቸት ስራ ይሰራበታል፡፡
  • በተቋቋሙና ደረጃቸው በተሻሻሉ ማህበረሰብ መረጃ ማዕከላት ድጋፍና ክትትል በማድረግ ስራ ፈላጊዎች የስራ ዕድል የመፍጠር፣ስራ ይሰራበታል፡፡
  • ለመንግስት መ/ቤቶች የአካባቢያዊ ኔትዎርክ (LAN) ዝርጋታ የማከናወን ስራ ይሰራበታል፡፡
  • የኢኮቴ መሳሪያዎች ለዕድሳት መለየትና እንዲሰበሰብ የማድረግ ስራ ይሰራበታል፡፡
  • የኢኮቴ መሳሪያዎች በመጠገን እና በማደስ ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ ይሰራበታል፡፡
  • የሶፍትዌርና የሀርድዌር የኢኮቴ መሳሪያዎች ጥገና የመጠገን ስራ ይሰራበታል፡፡
  • ከመንግስት መደበኛ የሚወጡ ወጪዎችን  ጥገናና እድሳት የማድረግ ስራ በመስራት የመንግስት ሃብት የማዳን ስራ ይሰራበታል፡፡
  • አዲስና ነባር ወረዳዎች/ተቋማት የወረዳኔት መሰረት ልማት አክቲቭ በማድርግ ከዞንና አቻ ወረዳዎች በቪዲዮ ኮንፈረንስ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ ይሰራበታል፡፡
  • 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የስኩልኔት ቴክኒካል ድጋፍ እንዲያገኙ የማድረግ ስራ ይሰራበታል፡፡
  • ለአዳዲስ ተቋማት የኔትወርክ መሰረተ ልማቶች የመዘርጋት፣ ተቋማት የኔትወርክ መሰረተ ልማት ማሻሻያ የማድረግ ስራ እና ተቋማት የኔትወርክ መሰረተ ልማት ጥገና የማድረግ ስራ የማድረግ ስራ ይሰራበታል፡፡

አቶ ሙባረክ አብዶ

የኢኮቴ መሠረተ ልማት ዝርጋታና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ