የመምሪያችን ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች እና ተቋማዊ ፍልስፍና

“በ2030 በዞናችን ውጤታማ የሆኑ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት የመማር፣የማልማት፣የመፍጠር፣የማላመድ እና የመጠቀም አቅም ተገንብቶ ማየት”

ለዞኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎችን ለህብረተሰቡ በአግባቡ በማልማት፣በመተግበርና በማስፋት ክልላዊ ብሎም ሀገራዊ የተወዳዳሪነት አቅምና በቴክኖሎጂ የዳበረ የአሰራር ስርዓት መፍጠር ነዉ፡፡

  • በጎ ህሊናና ቅን ልቦና፣
  • የስራ ፍቅርና ትጋት፣
  • ያልተገደበ አስተሳሰብና ምናባዊ ጉዞ፣
  • ለለውጥ በጋራ መስራት፤
  • ውጤታችንም ሆነ ውድቀታችን የጋራችን ነው፤
  • ችግር ፈቺነት፤
  • የማይረካ የመማር ጥማት፤
  • ለትውልድ የሚተላለፍ መሠረት፣
  • ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራርና ቀጣይነት ያለው መሻሻል፣
  • ዕውቀት ሀብት ነው
  • ለአዳዲስ ሀሳቦች ዕውቅና እንሰጣለን
  • ትጋት የአዎንታዊ ለውጥ ሀይል ነው
  • ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የአዲሱ ትውልድ ቋንቋ ነው
  • ኢኖቬሽንን ማበረታታት ለትውልድ ተስፋን መመገብ ነው
  • የዘመነ ዲጅታል ኢኮኖሚ የዕድገታችን መሰረት ነው